ወደ ጥገኝነት ፈላጊ መገልገያ ማእከል እንኳን ደህና መጡ። በማንም ተጽእኖ የለለብን የሰብአዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅት ነን። ለመንግሥት የምንሠራ ድርጅት አይደለንም። የምናቀርበው እርዳታ በነጻ ይሆናል። በአውስትራሊያ ውስጥ ጥገኝነት ለሚፈልጉ ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበርና እንዲጠበቅ እንረዳለን። ሰዎች በሞላ ነጻ መሆን እንዳለባቸው እናምናለን።
ጥገኝነት ፈላጊዎችን የምንረዳ ነን። ጥገኝነት ፈላጊ የሚሆን ሰው:
- በሃገራቸው ለመኖር በጣም አደገኛ በመሆኑ ከአገሩ መልቀቅ ያለበት እና
- በሃገራቸው ውስጥ በስጋት ላይ ላሉ ምክንያቱም በሚኖራቸው የጎሳ፣ የፖለቲካ ፍላጎት፣ ሃይማኖት፣ የትውልድ ዘር፣ የብሄር ዜግነት ወይም የማሕበራዊ ቡድን ሳቢያ ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰባቸው ወይም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ላሉ፣ እና
- ካለባቸው ከፍተኛ ጉዳት መንግሥታቸው ሊከላከልላቸው የማይችል ከሆነ ነው።
እንዴት ልንረዳዎ እንደምንችል
በአውስትራሊያ ውስጥ እርስዎ ስደተኛ መሆን ቀላል ላለመሆኑ ማረጋገጥ። በስደተኛ መልኩ ተቀባይነት ስለሚኖርዎ እድል ትክክለኛ የሆነ ህጋዊ ምክር በነጻ እናቀርብልዎታለን። ስደተኛ ለመሆን የሚችሉ መስሎ ካሰብን እንረዳዎታለን። ማንም ሰው ጥገኝነት ፈላጊ ለመሆን እንደማይመርጥ እናውቃለን ታዲያ ለዚህ ነው አስቸጋሪ ጊዜ ሲከሰት ባሉበት ቦታ ልንረዳዎ የምንገኘው።
እርስዎን ለመርዳት የተቻለንን ያህል እንጥራለን፤ ይህም በማንኛውም ነገር ማለት ህጋዊ የሆነ ምክር፣ የህክምና እንክብካቤ፣ መድሃኒቶች፣ ለልጅዎ የቅዘን ጨርቅ/ናፒ፣ በየቀኑ ጤናማ የሆኑ ምሳዎች፣ ሥራ ለመፈለግ እንዲሞክሩ ሊረዳ የሚችል በሜልበርን ውስጥ ስለሰፈራ መግለጫ ይቀርባል። የሚነግሩን ማንኛውም ነገር በሚስጢር ይጠበቃል እንዲሁም በማእከላችን ላይ ደህንነትዎ የተጠበቀ ይሆናል።
እንዴት ሊያገኙን እንደሚችሉ
214-218 Nicholson Street, Footscray, Victoria ይሆናል። እንዲሁም እርዳታ ለማግኘት በስልክ (03) 9326 6066 አድርጎ በተጠቀሱት ሰዓታት ውስጥ ሊደውሉልን ይችላሉ።
የጥገኝነት ፈላጊ መገልገያ ማእከልን በሚከተሉት ዘዴዎች ማግኘት ይችላሉ:
214-218 Nicholson Street, Footscray, Victoria
በአውስትራሊያ ሆነው በሜልበርን ውስጥ ካልሆኑስ ምን ይደረጋል?
በሜልበርን ውስጥ ላሉ ጥገኝነት ፈላጊዎች ብቻ መርዳት እንችላለን። በሌላ አስተዳደር ግዛት ውስጥ ከሆኑ በአቅራቢያዎ ያለን አገልግሎት ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ይጫኑ።
ከአውስትራሊያ ውጭ ከሆኑና በዓለም ዙሪያ ለጥገኝነት እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ መረጃ ከዚህ በታች ያለውን ማገናኛ ይጫኑ:
Connect with us
Need help from the ASRC? Call 03 9326 6066 or visit us: Mon-Tue-Thur-Fri 10am -5pm. Closed on Wednesdays.